ኖኣስ ማለት ምንድር ነው ?
ኖኣስ ማለት በኖርወይ ውስጥ ጥገኝነትን ለሚጠይቁት ግለሰቦች መብታቸው እንዲከበር የሚሰራ ገለልተኛ የሆነ ማለት ከመንግስት ተጽእኖ ነጻ የሆነ ድርጅት ነው፡ ፡ የኖኣስ ዋናው እንቅስቃሴ የሚያተኩረው መረጃና የሕግ ድጋፍን በመስጠትና እንዲሁም ውሳኔ በሚሰጡት ባለስልጣኖች ላይ ተሰሚነት እንዲያገኝ ጥረት ማድረግ ነው፡ ፡ የኖኣስ ዋና ዓላማ የጥገኝነት ጠያቒዎችን ጉዳይ በተመለከት የሚደረገው የፖለቲካ ውሳአኔና ኣተገባበሩ በሰብኣዊነትና በፍትህ የተመረኮስ እንዲሁም የዓለም ኣቀፍ ግደታን የትከትለ እንዲሆን ማስገንዘብና እንዲኡም ክትትል ማድረግ ነው፡ ፡
መረጃ ለጥገኝነት ጠያቂዎች
ኖኣስ በኖርወይ ጥገኝነትን ለሚጠይቁ መርጃና ምክር በመስጠት ይንቀሳቀሳል፡ ፡ የሚሰጠው መረጃም በኖርወይ ውስጥ ስለ ኣጠቃላይ የጥገኝነት ኣጠያይቅ ሂደትና እንዲሁም ጥገኝነትን የሚያሰጡ መመዘኛዎች ወይም መለኪያዎች እንዲሁም ስለ የጥገኝነት ጠያቂው መብትና ግዴታን በተመለከተ ይሆናል፡ ፡ ይህንን መረጃ በተመለከተ በመጽሄት መልክ ተዘጋጅቶ ስለሚገኝ ማንበብ ይቻላል፤ እሱም ከዚህ ስር እንደተመለከተው ተጽፎ ይገኛል፡ ፡
Informasjon til asylsøkere I Norge (PDF).
ለጥገኝነት ጠያቂዎች የህግ ድጋፍን ስለመስጠት
ጥገኝነት ጠያቂዎች በጉዳያቸው ላይ ከ UDI ወይም UNE ኣሉታዊ ውሳኔ ካግኙና እንዲሁም ይህንን ውሳኔ የሚመለከቱትን ሰነዶች ለኖኣስ ከላኩት ኖኣስ ደግሞ እነዚህን ሰነድች በጥሞና ይመለከታል፡ ፡ ከነዚህ ከቀረቡለት ሰነዶች ውስጥ የሆነ ተጨባጭ ያለው ጉዳይ ካጋጠመው ማለት ውሳነው ከኣሉታዊ ወደ ኣዎንታዊ ሊለወጥ ይችላል ብሎ ካመነበት በጥገኝነት ጠያቂው ስም ለውሳኔ ሰጭ ኣካላትን ደብዳቤ ይጽፋል፡ ፡ ይህንን የህግ ድጋፍ ልክ ጠበቃዎች ክሚያደርጉት ስራ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ፤ በተለይ በኖኣስ የሚደረገው የህግ ድጋፍ ግን በነጻ ላይ የተመሰረተ ነው፡ ፡
ኖኣስ የሚሰጥው ድጋፍ የጥገኝነትጥያቄ በተመለከተ ጉዳይ ብቻ ያተኮረ ነው፡ ፡ ይሁን እንጂ ቤተሰብን ስለ ማስመጣት በተመለከተ፤ ቪዛን ማግኘትን በተመለከተ፤ የኖርወጂያን ዜግነት ማግኘት ጥያቄ በተመለከተ ወይም ከኖርወይ ለቆ መውጣትን /መባረርን በተመለከተ ጉዳይ ግን Juss –Buss የተባለውን ድርጅት ጋር በመገናኘት እርዳታ መጠየቅ ይቻላል፡ ፡
በጉዳይህ ላይ በተመለከተ ከኖኣስ እርዳታ ማግኘትን ትፈልጋለህ ?
እርዳታን የምትሻ ከሆነ ጉዳይህን በሚመለከት ኣስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን ለኖኣስ መላክ ይኖርብሃል፡ ፡
ኖኣስ ጉዳይህን እንዲመለከትልህ ከፈለግህ ኣስፈላጊ የሆኑትን ሰነዶች ማለት ቃለመጠይቅ ያደረግህበትን ሰነድ፤ ከ UDI ፤ UNE የተሰጠህን ውሳኔ እና እንዲሁም ጠበቃህን የጻፈልህን የይግባኝ ሰነዶች ቅጅ ወይም ኮፒ ለኖኣስ መላክ ይኖርብሃል፡፡ ኣንዳንድ ኣስፈላጊ የምትላቸው ሰነዶች በእጅህ ከሌለህ በጠበቃህ ኣማካኝነት ማግኘት ትችላለህ፤ ካልቻልክ ደግሞ በኖኣስ ኣማክኝነት እንዲመጣልህ ለኖኣስ እርዳታ መጠየቅ ትችላለህ፡ ፡ ከላይ ከተጠቀሱት ውጭ ኣስፈላጊ የምትላቸው ሰነዶች ካሉህ ደግሞ ለኖኣስ መላክ ትችላልህ፡ ፡ ይህንን ስታደርግ ለኖኣስ የውክልና ስልጣን መስጠትህን የሚያመለክት ፎርም ሞልተህ መላክ ይኖርብሃል፤ እንዲሁም ኣሁን ያለህበትን ትክክለኛ ኣድራሻ ለኖኣስ መላክ ይኖርብሃል፡ ፡ ስለዚህ እላይ የተጠቀሱትን ሰንዶች እና የውክልና ስልጣን ሰነድን ኣንድ ላይ ኣድርገህ ለኖኣስ ላክልን፡ ፡ የውክልና ስልጣን ፎርም በኖርወጂያን እና በእንግልዝኛ ቁዋንቃ የተጻፈ ከዚህ በታች ማግኘት ትችላልህ፤
Fullmakt (PDF)
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሰነዶችህ ቀጥሎ በተመለከተው ኣድራሻ ወይም ፋክስ ቁጥር መላክ ትችላለህ፡
- NOAS, Torggata 22, 0183 Oslo
- Faksnummer ፡ 22 36 56 61
- ምን ያህል እርዳታ ከጠበቃህ እንዳግኘህ፡ ፡ ጠበቃህ እንደሚፈለገው ተገቢው እርዳታ ኣድርጎልህ ከሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ ኖኣስ ምንም ሊረዳህ ኣይችልም፡ ፡
- የተሰጠህን ኣሉታዊ ውሳኔ እንደገና በነዚህ ውሳኔ ሰጭ ኣካላት ታይቶ የሚለወጥበት ተጨባጭ መንገድ ካለ ኖኣስ ይገመግማል፡ ፡ ከዚህ በተረፈ ከይግባይ ሰሚ ኮሚቴ /UNE የሚሰጠው ኣሉታዊ ውሳኔ የመጨረሻ ስለሆነ ለመለወጡ በጣም ኣስቸጋሪ ነው፡ ፡ ምክንያቱም እነዚህ ባለስልጣኖች በውሳኒያቸው ላይ የጥገኝነት ፍቃድ ኣይገባውም ስለሆነም በኖርወይ ውስጥ መኖር ኣይችልም ብለው ስለሚወስኑ ነው፡ ፡
- ሌላው ነጥብ ምናልባት ጉዳይህን በሚመለከት ኣዲስ መረጃ ካለህ ማለት ከኣሁን ቀደም እነዚህ ውሳኔ ሰጭ ኣካላት ያላዩት ኣዲስ ነገር ካለህ እና ይህም ቀደም ሲል ለተሰጠው ውሳኔ ሊለውጠው ይችላል የሚል ነገር ካለ ኖኣስ ይገመግማል፡ ፡